መዝሙር
ምዕራፎች 36
መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም
የኀጥኡ ክፋት፣ የእግዚአብሔር በጎነት
ለመዘምራን አለቃ፤ የእግዚአብሔር ባሪያ የዳዊት መዝሙር
1ክፉውን ሰው፣በደል በልቡ ታናግረዋለች፤እግዚአብሔርን መፍራት፣በፊቱ የለም፤ 2በደሉ ግልጽ ወጥቶ እንዳይጠላ፣ራሱን በራሱ እጅግ ይሸነግላልና። 3ከአንደበቱ የሚወጣው የክፋትና የተንኰል ቃል ነው፤ማስተዋልንና በጎ ማድረግን ትቶአል። 4በመኝታው ላይ ክፋትን ያውጠነጥናል፤ራሱን በጎ ባልሆነ መንገድ ይመራል፤ክፋትንም አያርቅም። 5 እግዚአብሔር ሆይ፤ ምሕረትህ እስከ ሰማያት ይደርሳል፤ታማኝነትህም እስከ ጠፈር ይመጥቃል። 6ጽድቅህ እንደ ታላላቅ ተራሮች፣ፍርድህም እጅግ ጥልቅ ነው፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ሰውንም እንስሳንም ታድናለህ። 7አምላክ ሆይ፤ ምሕረትህ እንዴት ክቡር ነው!የሰዎች ልጆች ሁሉ፣በክንፎችህ ጥላ ሥር መጠጊያ ያገኛሉ። 8ከቤትህ ሲሳይ ይመገባሉ፤ከበረከትህም ወንዝ ይጠጣሉ። 9የሕይወት ምንጭ ከአንተ ዘንድ ነውና፤በብርሃንህም ብርሃንን እናያለን። 10ለሚያውቁህ ምሕረትህ፣ልባቸውም ለቀና ጽድቅህ ዘወትር አይቋረጥባቸው። 11የትዕቢተኛ እግር በላዬ አይምጣ፤የክፉውም ሰው እጅ አያሳደኝ። 12ክፉ አድራጊዎች እንዴት እንደ ወደቁና እንደ ተጋደሙ፣ቍልቍልም እንደ ተወረወሩና መነሣት እንደማይችሉ ተመልከት!ምዕራፎች
1
2
3
4
5
6
7
8
9
10
11
12
13
14
15
16
17
18
19
20
21
22
23
24
25
26
27
28
29
30
31
32
33
34
35
36
37
38
39
40
41
42
43
44
45
46
47
48
49
50
51
52
53
54
55
56
57
58
59
60
61
62
63
64
65
66
67
68
69
70
71
72
73
74
75
76
77
78
79
80
81
82
83
84
85
86
87
88
89
90
91
92
93
94
95
96
97
98
99
100
101
102
103
104
105
106
107
108
109
110
111
112
113
114
115
116
117
118
119
120
121
122
123
124
125
126
127
128
129
130
131
132
133
134
135
136
137
138
139
140
141
142
143
144
145
146
147
148
149
150