1 በተጨነቅሁ ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ተጣራሁ፤እርሱም መለሰልኝ።
2 እግዚአብሔር ሆይ፤ ከሐሰተኛ ከንፈር፣ከአታላይ ምላስም አድነኝ።
3 ሐሰተኛ አንደበት ሆይ፤ ምን ይከፈልህ?ከዚህስ የባሰ ምን ይደረግብህ?
4 በተሳለ የጦረኛ ቀስት፣በግራር ከሰል ፍም ይቀጣሃል።
5 በሜሼክ እኖራለሁና፣ በቄዳር ድንኳኖች መካከል እቀመጣለሁና ወዮልኝ!
6 ሰላምን በሚጠሉ መካከል፣ነፍሴ እጅግ ብዙ ጊዜ ኖረች።
7 እኔ ሰላም ፈላጊ ነኝ፤እነርሱ ግን በተናገርሁ ጊዜ ጠብ ይሻሉ።