1 እስራኤል እንዲህ ይበል፦“ከልጅነቴ ጀምሮ ብዙ ጊዜ አስጨነቁኝ፤
2 በርግጥ ከልጅነቴ ጀምሮ ብዙ ጊዜ አስጨነቁኝ፤ዳሩ ግን ድል አላደረጉኝም።
3 ዐራሾች ጀርባዬን ዐረሱት፤ትልማቸውንም አስረዘሙት።”
4 እግዚአብሔር ግን ጻድቅ ነው፤የክፉዎችን ገመድ በጣጥሶ ጣለው።
5 ጽዮንን የሚጠሉ ሁሉ፣ዐፍረው ወደ ኋላቸው ይመለሱ።
6 ገና ከመብቀሉ እንደሚደርቅ፣በጣራ ላይ እንደ በቀለ ሣር ይሁኑ፤
7 ደግሞም ለዐጫጅ እጁን፣ለነዶ ሰብሳቢ ዕቅፉን እንደማይሞላ ይሁኑ።
8 መንገድ ዐላፊዎችም፣“የእግዚአብሔር በረከት በእናንተ ላይ ይሁን፤ በእግዚአብሔር ስም እንባርካችኋለን” አይበሉ።