መዝሙር
ምዕራፎች 32
መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም
ግልጥ ኑዛዜ
የዳዊት ትምህርት
1መተላለፉ ይቅር የተባለለት፣ኀጢአቱም የተሸፈነለት፣እንዴት ቡሩክ ነው! 2 እግዚአብሔር ኀጢአቱን የማይቈጥርበት፣በመንፈሱም ሽንገላ የሌለበት ሰው፣እርሱ ቡሩክ ነው። 3ቀኑን ሙሉ ከመቃተቴ የተነሣ፣ዝም ባልሁ ጊዜ፣ዐጥንቶቼ ተበላሹ፤ 4በቀንና በሌሊት፣እጅህ ከብዳብኛለችና፤ኀይሌም የበጋ ትኵሳት እንደላሰው ነገር፣ከውስጤ ተሟጠጠ። ሴላ 5ኀጢአቴን ለአንተ አስታወቅሁ፤በደሌንም አልሸሸግሁም፤ደግሞም “መተላለፌን ለእግዚአብሔር እናዘዛለሁ” አልሁ፤አንተም የኀጢአቴን በደል፣ይቅር አልህ። ሴላ 6ስለዚህ ጻድቅ ሁሉ፣በጭንቅ ጊዜ ወደ አንተ ይጸልይ፤ኀይለኛ ጐርፍ አካባቢውን ቢያጥለቀልቅም፣እርሱ አጠገብ አይደርስም። 7አንተ መሸሸጊያዬ ነህ፤ከመከራ ትጠብቀኛለህ፤በድል ዝማሬም ትከበኛለህ። ሴላ 8አስተምርሃለሁ፤ በምትሄድበትም መንገድ እመራሃለሁ፤እመክርሃለሁ፤ በዐይኔም እከታተልሃለሁ። 9በልባብና በልጓም ካልተገሩ በቀር፣ወደ አንተ እንደማይቀርቡት፣ማስተዋል እንደሌላቸው፣እንደ ፈረስና እንደ በቅሎ አትሁኑ። 10የክፉዎች ዋይታ ብዙ ነው፤ በእግዚአብሔር የሚታመን ግን፣ምሕረት ይከበዋል። 11ጻድቃን ሆይ፤ በእግዚአብሔር ደስ ይበላችሁ፤ ሐሤትም አድርጉ፤ቅን ልብ ያላችሁም ሁሉ እልል በሉ።ምዕራፎች
1
2
3
4
5
6
7
8
9
10
11
12
13
14
15
16
17
18
19
20
21
22
23
24
25
26
27
28
29
30
31
32
33
34
35
36
37
38
39
40
41
42
43
44
45
46
47
48
49
50
51
52
53
54
55
56
57
58
59
60
61
62
63
64
65
66
67
68
69
70
71
72
73
74
75
76
77
78
79
80
81
82
83
84
85
86
87
88
89
90
91
92
93
94
95
96
97
98
99
100
101
102
103
104
105
106
107
108
109
110
111
112
113
114
115
116
117
118
119
120
121
122
123
124
125
126
127
128
129
130
131
132
133
134
135
136
137
138
139
140
141
142
143
144
145
146
147
148
149
150