1 ምድር ሁሉ ለእግዚአብሔር እልል በሉ፤
2 እግዚአብሔርን በደስታ አገልግሉት፤በፍስሓ ዝማሬ ፊቱ ቅረቡ።
3 እግዚአብሔር አምላክ መሆኑን ዕወቁ፤እርሱ ፈጠረን፤ እኛም የእርሱ ነን፤እኛ ሕዝቡ የማሰማሪያው በጎች ነን።
4 በምስጋና ወደ ደጆቹ፣በውዳሴም ወደ አደባባዮቹ ግቡ፤አመስግኑት፤ ስሙንም ባርኩ፤
5 እግዚአብሔር ቸር፣ ምሕረቱም ለዘላለም ነውና፤ታማኝነቱም ከትውልድ እስከ ትውልድ ነው።