መዝሙር
ምዕራፎች 77
መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም
የእስራኤል ጥንተ ነገር አሰላስሎ
ለመዘምራን አለቃ፤ ለኤዶታም፤ የአሳፍ መዝሙር
1ድምፄን ከፍ አድርጌ ወደ እግዚአብሔር ጮኽሁ፤ይሰማኝም ዘንድ ወደ አምላክ ጮኽሁ። 2በመከራዬ ቀን እግዚአብሔርን ፈለግሁት፤በሌሊትም ያለ ድካም እጆቼን ዘረጋሁ፤ነፍሴም አልጽናና አለች። 3አምላክ ሆይ፤ አንተን ባሰብሁ ቍጥር ቃተትሁ፤ባወጣሁ ባወረድሁም መጠን መንፈሴ ዛለች። ሴላ 4ዐይኖቼ እንዳይከደኑ ያዝሃቸው፤መናገር እስኪሳነኝ ድረስ ታወክሁ። 5የድሮውን ዘመን አሰብሁ፤የጥንቶቹን ዓመታት አውጠነጠንሁ። 6ዝማሬዬን በሌሊት አስታወስሁ፤ከልቤም ጋር ተጫወትሁ፤ መንፈሴም ተነቃቅቶ እንዲህ ሲል ጠየቀ፦ 7“ለመሆኑ፣ ጌታ ለዘላለም ይጥላልን?ከእንግዲህስ ከቶ በጎነትን አያሳይምን? 8ምሕረቱስ ለዘላለም ጠፋን?የገባውስ ቃል እስከ ወዲያኛው ተሻረን? 9እግዚአብሔር ቸርነቱን ዘነጋ?ወይስ ከቍጣው የተነሣ ርኅራኄውን ነፈገ?።” ሴላ 10እኔም፣ “የልዑል ቀኝ እጅ እንደ ተለወጠ ማሰቤ፣ይህ ድካሜ ነው” አልሁ። 11 የእግዚአብሔርን ሥራ አስታውሳለሁ፤የጥንት ታምራትህን በእርግጥ አስታውሳለሁ፤ 12ሥራህን ሁሉ አሰላስላለሁ፤ድንቅ ሥራህን ሁሉ አውጠነጥናለሁ። 13አምላክ ሆይ፤ መንገድህ ቅዱስ ነው፤እንደ አምላካችን ያለ ታላቅ አምላክ ማን ነው? 14ታምራትን የምታደርግ አምላክ አንተ ነህ፤በሕዝቦችም መካከል ኀይልህን ትገልጣለህ። 15የያዕቆብንና የዮሴፍን ልጆች፣ሕዝብህን በክንድህ ተቤዠሃቸው። ሴላ 16አምላክ ሆይ፤ ውሆች አዩህ፤ውሆች አንተን አይተው ተሸማቀቁ፤ጥልቆችም ተነዋወጡ። 17ደመናት ውሃን አንጠባጠቡ፤ሰማያት አንጐደጐዱ፤ፍላጾችህም ዙሪያውን አብለጨለጩ። 18የነጐድጓድህ ድምፅ በዐውሎ ነፋስ ውስጥ ተሰማ፤መብረቅህ ዓለምን አበራው፤ምድርም ራደች፤ ተንቀጠቀጠች። 19መንገድህ በባሕር ውስጥ ነው፤መሄጃህም በታላቅ ውሃ ውስጥ ነው፤ዱካህ ግን አልታወቀም። 20በሙሴና በአሮን እጅ፣ሕዝብህን እንደ በግ መንጋ መራኸው።ምዕራፎች
1
2
3
4
5
6
7
8
9
10
11
12
13
14
15
16
17
18
19
20
21
22
23
24
25
26
27
28
29
30
31
32
33
34
35
36
37
38
39
40
41
42
43
44
45
46
47
48
49
50
51
52
53
54
55
56
57
58
59
60
61
62
63
64
65
66
67
68
69
70
71
72
73
74
75
76
77
78
79
80
81
82
83
84
85
86
87
88
89
90
91
92
93
94
95
96
97
98
99
100
101
102
103
104
105
106
107
108
109
110
111
112
113
114
115
116
117
118
119
120
121
122
123
124
125
126
127
128
129
130
131
132
133
134
135
136
137
138
139
140
141
142
143
144
145
146
147
148
149
150