መዝሙር
ምዕራፎች 65
መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም
የምስጋና መዝሙር
ለመዘምራን አለቃ፤ የዳዊት የምስጋና መዝሙር
1እግዚአብሔር ሆይ፤ በጽዮን ለአንተ ውዳሴ ይገባል፤ለአንተ የተሳልነውን እንፈጽማለን። 2ጸሎትን የምትሰማ ሆይ፤የሰው ልጆች ሁሉ ወደ አንተ ይመጣሉ። 3ኀጢአት ባጥለቀለቀን ጊዜ፣አንተ መተላለፋችንን ይቅር አልህ። 4አንተ የመረጥኸው፣ ወደ ራስህ ያቀረብኸው፣በአደባባይህም ያኖርኸው ምስጉን ነው!ከተቀደሰው መቅደስህ፣ከቤትህም በረከት እንረካለን። 5እግዚአብሔር አዳኛችን ሆይ፤በጽድቅ ድንቅ አሠራር መልስልን፤አንተ ለምድር ዳርቻ ሁሉ፣በርቀት ላለውም ባሕር ተስፋ ነህ። 6ተራሮችን በብርታትህ መሠረትህ፤ኀይልንም ታጥቀሃል። 7አንተ የባሕሮችን ማስገምገም፣የማዕበላቸውን ፉጨት፣የሕዝቦችንም ሁከት ጸጥ ታደርጋለህ። 8ርቀው በምድር ዳርቻ ያሉት ከድንቅ ሥራህ የተነሣ ይደነግጣሉ፤የንጋትንና የምሽትን መምጫዎች፣በደስታ እልል እንዲሉ ታደርጋቸዋለህ። 9ምድርን ትጐበኛለህ፤ ታጠጣለህም፤እጅግ ታበለጽጋታለህም።ለሰዎች እህልን ይለግሱ ዘንድ፣የእግዚአብሔር ወንዞች ውሃን የተሞሉ ናቸው፤አንተ እንዲህ እንዲሆን ወስነሃልና። 10ትልሟን በውሃ ታረሰርሳለህ፤ቦይዋን ታስተካክላለህ፤በካፊያ ታለሰልሳለህ፤ቡቃያዋንም ትባርካለህ። 11ለዘመኑ በጎነትህን ታጐናጽፈዋለህ፤ሠረገላህም በረከትን ተሞልቶ ይፈስሳል። 12የምድረ በዳው ሣር እጅግ ለመለመ፤ኰረብቶችም ደስታን ተጐናጸፉ። 13ሜዳዎች መንጋ በመንጋ ሆኑ፤ሸለቆችም በእህል ተሸፈኑ፤እልል ይላሉ፤ ይዘምራሉም።ምዕራፎች
1
2
3
4
5
6
7
8
9
10
11
12
13
14
15
16
17
18
19
20
21
22
23
24
25
26
27
28
29
30
31
32
33
34
35
36
37
38
39
40
41
42
43
44
45
46
47
48
49
50
51
52
53
54
55
56
57
58
59
60
61
62
63
64
65
66
67
68
69
70
71
72
73
74
75
76
77
78
79
80
81
82
83
84
85
86
87
88
89
90
91
92
93
94
95
96
97
98
99
100
101
102
103
104
105
106
107
108
109
110
111
112
113
114
115
116
117
118
119
120
121
122
123
124
125
126
127
128
129
130
131
132
133
134
135
136
137
138
139
140
141
142
143
144
145
146
147
148
149
150