1 ነፍሴ ሆይ፤ እግዚአብሔርን ባርኪ፤ እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ፤ አንተ እጅግ ታላቅ ነህ፤ክብርንና ግርማን ለብሰሃል።
2 ብርሃንን እንደ ሸማ ተጐናጽፈሃል፤ሰማያትንም እንደ ድንኳን መጋረጃ ዘረጋህ፤
3 የእልፍኝህን አግዳሚ በውሆች ላይ አኖርህ፤ደመናትን ሠረገላህ አደረግህ፤በነፋስ ክንፍ ትሄዳለህ።
4 መላእክትህን መንፈስ፣አገልጋዮችህንም የእሳት ነበልባል ታደርጋለህ።