7 በገሠጽሃቸው ጊዜ ግን ፈጥነው ሄዱ፤የነጐድጓድህንም ድምፅ በሰሙ ጊዜ ሸሹ።
8 በተራሮች ላይ ፈሰሱ፤ወዳዘጋጀህላቸው ስፍራ፣ወደ ሸለቆዎች ወረዱ።
9 ተመልሰው ምድርን እንዳይሸፍኑ፣አልፈውም እንዳይመጡ ድንበር አበጀህላቸው።
10 ምንጮችን በሸለቆ ውስጥ እንዲሄዱ አደረግህ፤በተራሮችም መካከል ይፈሳሉ፤
11 የዱር እንስሳትም ከዚያ ይጠጣሉ፤የሜዳ አህዮችም ጥማቸውን ይቈርጣሉ።
12 የሰማይ ወፎች ጎጇቸውን በወንዞቹ ዳር ይሠራሉ፤በቅርንጫፎችም መካከል ይዘምራሉ።
13 ከላይ ከእልፍኝህ ተራሮችህን ታጠጣለህ፤ምድርም በሥራህ ፍሬ ትረካለች።