1 እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ስሙንም ጥሩ፤ሥራውንም በሕዝቦች መካከል ግለጡ።
2 ተቀኙለት፤ ዘምሩለት፤ድንቅ ሥራዎቹንም ሁሉ ተናገሩ።
3 በቅዱስ ስሙ ተጓደዱ፤ እግዚአብሔርን የሚሹት ልባቸው ደስ ይበለው።
4 እግዚአብሔርንና ብርታቱን ፈልጉ፤ፊቱንም ዘወትር ፈልጉ።
5 ያደረጋቸውን ድንቅ ሥራዎች፣ታምራቱንና ከአፉ የወጣውን ፍርድ አስቡ፤