16 በምድሪቱ ላይ ራብን ጠራ፤የምግብንም አቅርቦት ሁሉ አቋረጠ፤
17 በባርነት የተሸጠውን ሰው፣ዮሴፍን ከእነርሱ አስቀድሞ ላከ።
18 እግሮቹ በእግር ብረት ተላላጡ፤በዐንገቱም የብረት ማነቆ ገባ።
19 የተናገረው ቃል እስኪፈጸምለት፣ የእግዚአብሔር ቃል ፈተነው።
20 ንጉሥ ልኮ አስፈታው፤የሕዝቦችም ገዥ ነጻ አወጣው።
21 የቤቱ ጌታ፣የንብረቱም ሁሉ አስተዳዳሪ አደረገው፤
22 ይኸውም ሹማምቱን በራሱ መንገድ ይመራ ዘንድ፣ታላላቆቹንም ጥበብ ያስተምር ዘንድ ነበር።