26 ባሪያውን ሙሴን፣የመረጠውንም አሮንን ላከ።
27 እነርሱም ታምራታዊ ምልክቶችን በመካከላቸው፣ድንቅ ነገሮቹንም በካም ምድር አደረጉ።
28 ጨለማን ልኮ ምድሪቱን ጽልመት አለበሰ፤እነርሱም በቃሉ ላይ ማመፅን ተዉ።
29 ውሃቸውን ወደ ደም ለወጠ፤ዓሦቻቸውንም ፈጀ።
30 ምድራቸውም፣ የነገሥታታቸው እልፍኝ ሳይቀር፣ጓጒንቸር ተርመሰመሰባቸው።
31 እርሱ በተናገረ ጊዜ የዝንብ መንጋ መጣ፤ትንኞችም ምድራቸውን ወረሩ።
32 ዝናባቸውን በረዶ አደረገው፤ምድራቸውም ሁሉ መብረቅ አወረደ።