11 ያለውን ሁሉ ዕዳ ጠያቂ ይውረሰው፤የድካሙንም ዋጋ ባዕዳን ይቀሙት።
12 ማንም ሰው ምሕረት አያድርግለት፤ለድኻ አደግ ልጆቹም የሚራራ አይኑር።
13 ዘሩ ተለይቶ ይጥፋ፤ስማቸውም በሚቀጥለው ትውልድ ይደምሰስ።
14 የአባቶቹ በደል በእግዚአብሔር ፊት ይታሰብ፤የእናቱም ኀጢአት አይደምሰስ።
15 መታሰቢያቸውን ከምድር ያጠፉ ዘንድ፣ኀጢአታቸው ሁል ጊዜ በእግዚአብሔር ፊት ይኑር፤
16 ችግረኛውንና ምስኪኑን፣ ልቡም የቈሰለውን፣እስከ ሞት አሳደደ እንጂ፣ምሕረት ያደርግ ዘንድ አላሰበምና።
17 መራገምን ወደደ፤ ወደ እርሱም መጣች፤በመባረክ ደስ አልተሰኘም፤በረከትም ከእርሱ ራቀች።