1 እስራኤል ከግብፅ ወጥቶ ሲሄድ፣የያዕቆብም ቤት ቋንቋው ልዩ ከሆነ ሕዝብ ተለይቶ ሲወጣ፣
2 ይሁዳ የእግዚአብሔር መቅደስ፣እስራኤልም ግዛቱ ሆነ።
3 ባሕር አየች፤ ሸሸችም፤ዮርዳኖስም ወደ ኋላው ተመለሰ።
4 ተራሮች እንደ አውራ በግ፣ኰረብቶችም እንደ ጠቦት ዘለሉ።
5 አንቺ ባሕር፤ የሸሸሽው አንቺም ዮርዳኖስ ያፈገፈግሽው ለምንድን ነው?
6 እናንተ ተራሮች እንደ አውራ በግ፣ኰረብቶችም እንደ ጠቦት ለምን ዘለላችሁ?
7 ምድር ሆይ፤ በጌታ ፊት፣በያዕቆብ አምላክ ፊት ተንቀጥቀጪ፤