9 እኔም በሕያዋን ምድር፣ በእግዚአብሔር ፊት እመላለሳለሁ።
10 “እጅግ ተጨንቄአለሁ” ባልሁበት ጊዜ እንኳ፣እምነቴን ጠብቄአለሁ።
11 ግራ በተጋባሁ ጊዜ፣“ሰው ሁሉ ሐሰተኛ ነው” አልሁ።
12 ስለ ዋለልኝ ውለታ ሁሉ፣ ለእግዚአብሔር ምን ልክፈለው?
13 የመዳንን ጽዋ አነሣለሁ፤ የእግዚአብሔርንም ስም እጠራለሁ።
14 በሕዝቡ ሁሉ ፊት፣ስእለቴን ለእግዚአብሔር እፈጽማለሁ።
15 የቅዱሳኑ ሞት፣ በእግዚአብሔር ፊት የተከበረ ነው።