23 እግዚአብሔር ይህን አደረገ፤ለዐይናችንም ድንቅ ናት።
24 እግዚአብሔር የሠራት ቀን ይህች ናት፤በእርሷ ሐሤት እናድርግ፤ ደስም ይበለን።
25 እግዚአብሔር ሆይ፤ እባክህ አድነን፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ እባክህ አሳካልን።
26 በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ ቡሩክ ነው። ከእግዚአብሔር ቤት ባረክናችሁ።
27 እግዚአብሔር አምላክ ነው፤ብርሃኑንም በላያችን አበራ፤እስከ መሠዊያው ቀንዶች ድረስ በመውጣት፣ዝንጣፊ ይዛችሁ በዓሉን ከሚያከብሩት ጋር ተቀላቀሉ።
28 አንተ አምላኬ ነህ፤ አመሰግንሃለሁ፤አንተ አምላኬ ነህ፤ ከፍ ከፍ አደርግሃለሁ።
29 ቸር ነውና፣ እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ምሕረቱም ለዘላለም ጸንታ ትኖራለች።