1 ዐይኖቼን ወደ ተራሮች አነሣሁ፤ረድኤቴ ከወዴት ይመጣል?
2 ረድኤቴ ሰማይንና ምድርን ከፈጠረ፣ ከእግዚአብሔር ዘንድ ይመጣል።
3 እግርህ እንዲሸራተት አይፈቅድም፤የሚጠብቅህም አይተኛም።
4 እነሆ፤ እስራኤልን የሚጠብቅ፣ አይተኛም፤ አያንቀላፋምም።
5 እግዚአብሔር ይጠብቅሃል፤ እግዚአብሔር በቀኝህ በኩል ይከልልሃል።
6 ፀሓይ በቀን አያቃጥልህም፤ጨረቃም በሌሊት ጒዳት አታመጣብህም።
7 እግዚአብሔር ከክፉ ሁሉ ይጠብቅሃል፤ነፍስህንም ይንከባከባታል።
8 እግዚአብሔር ከአሁን ጀምሮ እስከ ዘላለም፣መውጣትህንና መግባትህን ይጠብቃል።