1 “ወደ እግዚአብሔር ቤት እንሂድ” ባሉኝ ጊዜ፣ደስ አለኝ።
2 ኢየሩሳሌም ሆይ፤ እግሮቻችን ከደጅሽ ውስጥ ቆመዋል።
3 ኢየሩሳሌም እጅግ እንደ ተጠጋጋች፣ከተማ ሆና ተሠርታለች።
4 ለእስራኤል በተሰጠው ሥርዐት መሠረት፣ የእግዚአብሔርን ስም ለማመስገን፣ የእግዚአብሔር ነገዶች፣ወደዚያ ይመጣሉ።
5 በዚያም የፍርድ ዙፋኖች የሆኑት፣የዳዊት ቤት ዙፋኖች ተዘርግተዋል።
6 እንዲህ ብላችሁ ለኢየሩሳሌም ሰላም ጸልዩ፤“የሚወዱሽ ይለምልሙ፤
7 በቅጥርሽ ውስጥ ሰላም ይሁን፤በምሽግሽም ውስጥ መረጋጋት ይስፈን”።