1 ወንድሞች ተስማምተው በአንድነት ሲኖሩ፣እንዴት መልካም ነው! ምንኛስ ደስ ያሰኛል!
2 በራስ ላይ ፈሶ፣እስከ ጢም እንደሚዘልቅ፣እስከ አሮን ጢም እንደሚወርድ፣እስከ ልብሱም ዐንገትጌ እንደሚደርስ ውድ ሽቱ ነው።
3 ደግሞም በጽዮን ተራራ ላይ እንደሚወርድ፣እንደ አርሞንዔም ጠል ነው፤በዚያ እግዚአብሔር በረከቱን፣ሕይወትንም እስከ ዘላለም አዞአልና።