1 እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ቸር ነውና፤ምሕረቱ ለዘላለም ነውና።
2 የአማልክትን አምላክ አመስግኑ፤ምሕረቱ ለዘላለም ነውና።
3 የጌቶችን ጌታ አመሰግኑ፤ምሕረቱ ለዘላለም ነውና።
4 እርሱ ብቻውን ታላላቅ ታምራትን የሚያደርግ፤ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
5 ሰማያትን በብልኀት የሠራ፤ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
6 ምድርን በውሃ ላይ የዘረጋ፤ምሕረቱ ለዘላለም ነውና።
7 ታላላቅ ብርሃናትን የሠራ፤ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
8 ፀሓይ በቀን እንዲሠለጥን ያደረገ፤ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
9 ጨረቃና ከዋክብት በሌሊት እንዲሠለጥኑ ያደረገ፤ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
10 የግብፅን በኵር የመታ፤ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
11 እስራኤልን ከመካከላቸው ያወጣ፤ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
12 በኀያል እጅና በተዘረጋች ክንድ ይህን ያደረገ፤ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
13 የኤርትራን ባሕር ለሁለት የከፈለ፤ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
14 እስራኤልን በመካከሉ ያሳለፈ፤ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
15 ፈርዖንንና ሰራዊቱን በኤርትራ ባሕር ያሰጠመ፤ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
16 ሕዝቡን በምድረ በዳ የመራ፤ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
17 ታላላቅ ነገሥታትን የመታ፤ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
18 ኀያላን ነገሥታትን የገደለ፤ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
19 የአሞራውያንን ንጉሥ ሴዎንን የገደለ፤ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
20 የባሳንን ንጉሥ ዐግን የገደለ፤ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
21 ምድራቸውን ርስት አድርጎ የሰጠ፤ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
22 ለባሪያው ለእስራኤል ርስት አድርጎ የሰጠ፤ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
23 በውርደታችን ጊዜ ያሰበን፤ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
24 ከጠላቶቻችን እጅ ያዳነን፤ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
25 ለፍጡር ሁሉ ምግብን የሚሰጥ፤ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
26 የሰማይን አምላክ አመስግኑ፤ምሕረቱ ለዘላለም ነውና።