1 ሃሌ ሉያ።አምላካችንን በመዝሙር ማወደስ እንዴት መልካም ነው፤እርሱን ማመስገን ደስ ያሰኛል፤ ይህ ተገቢም ነው።
2 እግዚአብሔር ኢየሩሳሌምን መልሶ ይሠራታል፤ከእስራኤል የተበተኑትን ይሰበስባል።
3 ልባቸው የተሰበረውን ይፈውሳል፤ቍስላቸውንም ይጠግናል።
4 የከዋክብትን ብዛት ያውቃል፤እያንዳንዱንም በስሙ ይጠራዋል።
5 ጌታችን ታላቅ ነው፤ እጅግ ኀያልም ነው፤ለጥበቡም ወሰን የለውም።