1 ሃሌ ሉያ። እግዚአብሔርን በመቅደሱ አመስግኑት፤በታላቅ ጠፈሩ አወድሱት።
2 ስለ ብርቱ ሥራው አመስግኑት፤እጅግ ታላቅ ነውና ወድሱት።
3 በመለከት ድምፅ አመስግኑት፤በበገናና በመሰንቆ ወድሱት።
4 በከበሮና በሽብሸባ አመስግኑት፤በባለ አውታር መሣሪያና በእምቢልታ አወድሱት።
5 ተርገብጋቢ ድምፅ ባለው ጸናጽል አመስግኑት፤ድምፀ መልካም በሆነ ጸናጽል ወድሱት።