3 በምድር ያሉ ቅዱሳን፣ሙሉ ደስታ የማገኝባቸው ክቡራን ናቸው።
4 ሌሎችን አማልክት የሚከተሉ፣ሐዘናቸው ይበዛል፤እኔ ግን የደም ቍርባናቸውን አላፈስም፤ስማቸውንም በአፌ አልጠራም፤
5 እግዚአብሔር የርስት ድርሻዬና ጽዋዬ ነው፤ዕጣዬም በእጅህ ናት።
6 መካለያ ገመድ ባማረ ስፍራ ተጥሎልኛል፤በርግጥም የተዋበች ርስት አግኝቻለሁ።
7 የሚመክረኝን እግዚአብሔርን እባርካለሁ፤በሌሊት እንኳ ልቤ ቀናውን ያመላክተኛል።
8 እግዚአብሔርን ሁል ጊዜ በፊቴ አድርጌአለሁ፤እርሱ በቀኜ ስላለ አልናወጥም።
9 ስለዚህ ልቤ ደስ አለው፤ ነፍሴም ሐሤት አደረገች፤ሥጋዬም ያለ ሥጋት ዐርፎ ይቀመጣል፤