4 በሰማይ ዙፋን ላይ የተቀመጠው ይሥቃል፤ጌታም ይሣለቅባቸዋል።
5 ከዚያም በቊጣው ይናገራቸዋል፤በመዓቱም ያስደነግጣቸዋል፤
6 ደግሞም፣ “እኔ ግን በተቀደሰው ተራራዬ፣በጽዮን ላይ የራሴን ንጉሥ ሾምሁ” ይላል።
7 የእግዚአብሔርን ሕግ ዐውጃለሁ፤እርሱም እንዲህ አለኝ፤ “አንተ ልጄ ነህ፤እኔ ዛሬ ወለድሁህ፤
8 ለምነኝ፤መንግሥታትን ርስት አድርጌ፣የምድርንም ዳርቻ ግዛት እንዲሆንህ እሰጥሃለሁ።
9 አንተም በብረት በትር ትቀጠቅጣቸዋለህ፤እንደ ሸክላ ዕቃ ታደቃቸዋለህ።”
10 ስለዚህ እናንት ነገሥታት ልብ በሉ፤እናንት የምድር ገዦችም፣ ተጠንቀቁ።