5 መንፈሴን በእጅህ ዐደራ እሰጣለሁ፤ እግዚአብሔር የእውነት አምላክ ሆይ፤አንተ ተቤዠኝ።
6 ለከንቱ ጣዖታት ስፍራ የሚሰጡትን ጠላሁ፤ነገር ግን በእግዚአብሔር ታመንሁ።
7 በምሕረትህ ደስ እሰኛለሁ፤ ሐሤትም አደርጋለሁ፤መከራዬን አይተሃልና፤የነፍሴንም ጭንቀት ዐውቀሃል።
8 ለጠላት አሳልፈህ አልሰጠኸኝም፤ነገር ግን እግሮቼን ሰፊ ቦታ ላይ አቆምሃቸው።
9 እግዚአብሔር ሆይ፤ በመከራ ውስጥ ነኝና ማረኝ፤ዐይኖቼ በሐዘን ደክመዋል፤ነፍስና ሥጋዬም ዝለዋል።
10 ሕይወቴ በመጨነቅ፣ዕድሜዬም በመቃተት ዐለቀ፤ከመከራዬ የተነሣ ጒልበት ከዳኝ፤ዐጥንቴም በውስጤ ሟሟ።
11 ከጠላቶቼ ሁሉ የተነሣ፣ለጎረቤቶቼ መዘባበቻ፣ለወዳጆቼ መሣለቂያ ሆኛለሁ፤መንገድ ላይ የሚያገኙኝም ይሸሹኛል።