2 እግዚአብሔር ኀጢአቱን የማይቈጥርበት፣በመንፈሱም ሽንገላ የሌለበት ሰው፣እርሱ ቡሩክ ነው።
3 ቀኑን ሙሉ ከመቃተቴ የተነሣ፣ዝም ባልሁ ጊዜ፣ዐጥንቶቼ ተበላሹ፤
4 በቀንና በሌሊት፣እጅህ ከብዳብኛለችና፤ኀይሌም የበጋ ትኵሳት እንደላሰው ነገር፣ከውስጤ ተሟጠጠ። ሴላ
5 ኀጢአቴን ለአንተ አስታወቅሁ፤በደሌንም አልሸሸግሁም፤ደግሞም “መተላለፌን ለእግዚአብሔር እናዘዛለሁ” አልሁ፤አንተም የኀጢአቴን በደል፣ይቅር አልህ። ሴላ
6 ስለዚህ ጻድቅ ሁሉ፣በጭንቅ ጊዜ ወደ አንተ ይጸልይ፤ኀይለኛ ጐርፍ አካባቢውን ቢያጥለቀልቅም፣እርሱ አጠገብ አይደርስም።
7 አንተ መሸሸጊያዬ ነህ፤ከመከራ ትጠብቀኛለህ፤በድል ዝማሬም ትከበኛለህ። ሴላ
8 አስተምርሃለሁ፤ በምትሄድበትም መንገድ እመራሃለሁ፤እመክርሃለሁ፤ በዐይኔም እከታተልሃለሁ።