15 የእግዚአብሔር ዐይኖች ወደ ጻድቃን ናቸው፤ጆሮዎቹም ለጩኸታቸው ክፍት ናቸው።
16 መታሰቢያቸውን ከምድር ለማጥፋት፣ የእግዚአብሔር ፊት በክፉ አድራጊዎች ላይ ነው።
17 ጻድቃን ሲጮኹ፣ እግዚአብሔር ይሰማቸዋል፤ከመከራቸውም ሁሉ ያድናቸዋል።
18 እግዚአብሔር ልባቸው ለተሰበረ ቅርብ ነው፤መንፈሳቸው የተሰበረውንም ያድናቸዋል።
19 የጻድቅ መከራው ብዙ ነው፤ እግዚአብሔር ግን ከሁሉም ያድነዋል።
20 ዐጥንቶቹን ሁሉ ይጠብቃል፤ከእነርሱም አንድ አይሰበርም።
21 ኀጢአተኞችን ክፋት ይገድላቸዋል፤ጻድቃንን የሚጠሉ ይፈረድባቸዋል።