5 ወደ እርሱ የሚመለከቱ ያበራሉ፤ፊታቸውም ከቶ አያፍርም።
6 ይህ ችግረኛ ጮኸ፤ እግዚአብሔርም ሰማው፤ከመከራውም ሁሉ አዳነው።
7 እግዚአብሔርን በሚፈሩት ዙሪያ የእግዚአብሔር መልአክ ይሰፍራል፤ያድናቸዋልም።
8 እግዚአብሔር ቸር መሆኑን ቀምሳችሁ እዩ፤እርሱን መጠጊያ የሚያደርግ ምንኛ ቡሩክ ነው!
9 እናንተ ቅዱሳኑ፤ እግዚአብሔርን ፍሩት፤እርሱን የሚፈሩት አንዳች አያጡምና።
10 አንበሶች ሊያጡ፣ ሊራቡም ይችላሉ፤ እግዚአብሔርን የሚሹ ግን መልካም ነገር አይጐድልባቸውም።
11 ልጆቼ ሆይ፣ ኑ፤ ስሙኝ፤ እግዚአብሔርን መፍራት አስተምራችኋለሁ።