1 አምላክ ሆይ፤ ፍረድልኝ፤ከጽድቅ ከራቀ ሕዝብ ጋር ተሟገትልኝ፤ከአታላዮችና ከክፉዎች ሰዎችም አድነኝ።
2 አምላክ ሆይ፤ አንተ ብርታቴ ነህና፣ለምን ተውኸኝ?ጠላትስ እያስጨነቀኝ፣ለምን በሐዘን እመላለሳለሁ?
3 ብርሃንህንና እውነትህን ላክ፤እነርሱ ይምሩኝ፤ወደ ተቀደሰው ተራራህ፣ወደ ማደሪያህ ያድርሱኝ።
4 እኔም ወደ እግዚአብሔር መሠዊያ አቀናለሁ፤ፍጹም ደስታዬ ወደ ሆነው አምላክ እሄዳለሁ፤እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ፣በበገና አመሰግንሃለሁ።