15 ውርደቴ ቀኑን ሙሉ በፊቴ ነው፤ፊቴም ዕፍረትን ተከናንቦአል።
16 ይህም ከሚዘልፍና ከሚያላግጥ ሰው ድምፅ የተነሣ፣ከጠላትና ከተበቃይ ሁኔታ የተነሣ ነው።
17 አንተን ሳንረሳ፣ለኪዳንህም ታማኝነታችንን ሳናጓድል፣ይህ ሁሉ ደረሰብን።
18 ልባችን ወደ ኋላ አላለም፤እግራችንም ከመንገድህ አልወጣም።
19 አንተ ግን ተኵላዎች በሚውሉበት ቦታ ሰባብረህ ጣልኸን፤በሞት ጥላም ሸፈንኸን።
20 የአምላካችንን ስም ረስተን፣እጃችንንም ወደ ባዕድ አምላክ ዘርግተን ቢሆን ኖሮ፣
21 እግዚአብሔር ይህን ማወቅ ይሳነዋልን?እርሱ ልብ የሰወረውን የሚረዳ ነውና።