6 አምላካችንን አወድሱት፤ አወድሱት፤ንጉሣችንን አወድሱት፤ አወድሱት፤
7 እግዚአብሔር የምድር ሁሉ ንጉሥ ነውና፤ምርጥ ዝማሬ አቅርቡለት።
8 እግዚአብሔር በሕዝቦች ላይ ነግሦአል፤እግዚአብሔር በተቀደሰ ዙፋኑ ላይ ተቀምጦአል።
9 ከአብርሃም አምላክ ሕዝብ ጋር፣የሕዝቦች መኳንንት ተሰበሰቡ፤የምድር ነገሥታት የእግዚአብሔር ናቸውና፤እርሱም እጅግ ከፍ ከፍ ያለ ነው።