3 እግዚአብሔር ሆይ፤ በማለዳ ድምፄን ትሰማለህ፤በማለዳ ልመናዬን በፊትህ አቀርባለሁ፤ፈቃድህንም በጥሞና እጠባበቃለሁ፤
4 አንተ በክፋት ደስ የምትሰኝ አምላክ አይደለህም፤ክፉም ከአንተ ጋር አያድርም።
5 እብሪተኞች በፊትህ መቆም አይችሉም፤ክፉ አድራጊዎችንም ሁሉ ጠላህ።
6 ሐሰት የሚናገሩትን ታጠፋቸዋለህ፤ደም የተጠሙትንና አታላዮችን፣ እግዚአብሔር ይጸየፋቸዋል።
7 እኔ ግን በምሕረትህ ብዛትወደ ቤትህ እገባለሁ፤አንተንም በመፍራት፣ወደ ተቀደሰው መቅደስህ እሰግዳለሁ።
8 እግዚአብሔር ሆይ፤ ከጠላቶቼ የተነሣ፣በጽድቅህ ምራኝ፤መንገድህንም በፊቴ አቅናልኝ።
9 በንግግራቸው ውስጥ እውነት የለም፤ልባቸው የጥፋት ጐሬ ነው፤ጒሮሮአቸው የተከፈተ መቃብር ነው፤በምላሳቸውም ይሸነግላሉ።