18 ሌባውን ስታይ አብረኸው ነጐድህ፤ዕድል ፈንታህንም ከአመንዝሮች ጋር አደረግህ።
19 አፍህን ለክፋት አዋልህ፤አንደበትህም ሽንገላን ጐነጐነ።
20 ተቀምጠህ ወንድምህን አማኸው፤የእናትህንም ልጅ ስም አጐደፍህ።
21 ይህን አድርገህ ዝም አልሁ፤እንዳንተ የሆንሁ መሰለህ።አሁን ግን እገሥጽሃለሁ፣ፊት ለፊትም እወቅስሃለሁ።
22 “እናንተ እግዚአብሔርን የምትረሱ፤ ይህን ልብ በሉ፤አለበለዚያ ብትንትናችሁን አወጣለሁ፤የሚያድናችሁም የለም።
23 የምስጋናን መሥዋዕት የሚሠዋ ያከብረኛል፤መንገዱንም ቀና ለሚያደርግ፣የእግዚአብሔርን ማዳን አሳየዋለሁ።”