11 ጥፋት በመካከሏ ይገኛል፤ግፍና አታላይነትም ከጎዳናዋ አይጠፋም።
12 የሚዘልፈኝ ጠላት አይደለምና፤ቢሆንማ ኖሮ በታገሥሁት ነበር፤የሚጠላኝ፣ ራሱንም ቀና ቀና ያደረገብኝ ባላንጣ አይደለም፤ቢሆንማ ከእርሱ በተሸሸግሁ ነበር።
13 ነገር ግን አድራጊው አንተ ነህ፤ እኩያዬ፣ ባልንጀራዬና ወዳጄ፤
14 በእግዚአብሔርም ቤት አብረን በሕዝብ መካከል ተመላለስን፤ደስ የሚል ፍቅር በአንድነት ነበረን።
15 ሞት ሳይታሰብ ድንገት ይምጣባቸው፤በሕይወት ሳሉ ወደ ሲኦል ይውረዱ፤ክፋት በመካከላቸው አድራለችና።
16 እኔ ግን ወደ እግዚአብሔር እጣራለሁ፤ እግዚአብሔርም ያድነኛል።
17 በማታ፣ በጥዋትና በቀትር፣እጮኻለሁ፤ እቃትታለሁም፤እርሱም ድምፄን ይሰማል።