4 ልቤ በውስጤ ተጨነቀብኝ፤የሞት ድንጋጤም በላዬ መጣ።
5 ፍርሀትና እንቅጥቃጤ መጣብኝ፤ሽብርም ዋጠኝ።
6 እኔም እንዲህ አልሁ፤ “ምነው የርግብ ክንፍ በኖረኝ!በርሬ በሄድሁና ባረፍሁ ነበር፤
7 እነሆ፤ ኰብልዬ በራቅሁ፣በምድረ በዳም በሰነበትሁ ነበር፤ ሴላ
8 ከዐውሎ ነፋስና ከውሽንፍር ሸሽቼ፣ወደ መጠለያዬ ፈጥኜ በደረስሁ ነበር።”
9 ጌታ ሆይ፤ ግፍንና ሁከትን በከተማዪቱ ውስጥ አይቼአለሁና፣ግራ አጋባቸው፤ ቋንቋቸውንም ደበላልቅ።
10 ቀንና ሌሊት ቅጥሯ ላይ ወጥተው ይዞሯታል፤ተንኰልና መከራ በውስጧ አለ።