4 ቃሉን በማመሰግነው አምላክ፣በእግዚአብሔር ታምኛለሁ፤ አልፈራም፤ሥጋ ለባሽ ምን ሊያደርገኝ ይችላል?
5 ቀኑን ሙሉ ቃሌን ያጣምሙታል፤ዘወትርም ሊጐዱኝ ያሤራሉ።
6 ይዶልታሉ፤ ያደባሉ፤ርምጃዬን ይከታተላሉ፤ነፍሴንም ለማጥፋት ይሻሉ።
7 እግዚአብሔር ሆይ፤ ከቶ እንዳያመልጡ፣ሕዝቦቹን በቍጣህ ጣላቸው።
8 ሰቆቃዬን መዝግብ፤እንባዬን በዕቃህ አጠራቅም፤ሁሉስ በመዝገብህ የተያዘ አይደለምን?
9 ወደ አንተ በተጣራሁ ቀን፣ጠላቶቼ ወደ ኋላቸው ይመለሳሉ፤በዚህም፣ አምላክ ከጐኔ መቆሙን ዐውቃለሁ።
10 ቃሉን በማመሰግነው አምላክ፣ቃሉን በማመሰግነው በእግዚአብሔር፣