3 እግዚአብሔርን እንዲህ በሉት፤ “ሥራህ እንዴት ግሩም ነው!ጠላቶችህ ከኀይልህ ታላቅነት የተነሣ፣በፊትህ ይርዳሉ።
4 ምድር ሁሉ ይሰግድልሃል፤በዝማሬ ያመሰግኑሃል፤ለስምህም ይዘምራሉ። ሴላ
5 ኑና፣ እግዚአብሔር ያደረገውን እዩበሰዎች መካከል ሥራው አስፈሪ ነው!
6 ባሕሩን የብስ አደረገው፤ወንዙን በእግር ተሻገሩ፤ኑ፣ በእርሱ ደስ ይበለን።
7 በኀይሉ ለዘላለም ይገዛል፤ዐይኖቹ ሕዝቦችን ይመለከታሉ፤እንግዲህ ዐመፀኞች ቀና ቀና አይበሉ። ሴላ
8 ሕዝቦች ሆይ፤ አምላካችንን ባርኩ፤የምስጋናውንም ድምፅ አሰሙ።
9 እኛን በሕይወት የሚያኖረን፣እግራችንንም ከመንሸራተት የሚጠብቅ እርሱ ነው።