1 እግዚአብሔር ይማረን፤ ይባርከን፤ፊቱንም በላያችን ያብራ፤ ሴላ
2 መንገድህ በምድር ላይ፣ማዳንህም በሕዝቦች ሁሉ መካከል ይታወቅ ዘንድ።
3 እግዚአብሔር ሆይ፤ ሰዎች ያመስግኑህ፤ሰዎች ሁሉ ምስጋና ያቅርቡልህ።
4 ለሕዝቦች በቅን ስለምትፈርድላቸው፣ሰዎችንም በምድር ላይ ስለምትመራ፣ሕዝቦች ደስ ይበላቸው፤ በእልልታም ይዘምሩ። ሴላ