19 የደረሰብኝን ስድብ፣ ዕፍረትና ውርደት ታውቃለህ፤ጠላቶቼንም አንድ በአንድ ታውቃቸዋለህ።
20 ስድብ ልቤን ጐድቶታል፤ተስፋዬም ተሟጦአል፤አስተዛዛኝ ፈለግሁ፤ አላገኘሁምም፤አጽናኝም ፈለግሁ፤ አንድም አልነበረም።
21 ምግቤን ከሐሞት ቀላቀሉ፤ለጥማቴም ሆምጣጤ ሰጡኝ።
22 የቀረበላቸው ማእድ ወጥመድ ይሁንባቸው፤ለማኅበራቸውም አሽክላ ይሁን።
23 ዐይኖቻቸው እንዳያዩ ይጨልሙ፤ጀርባቸውም ዘወትር ይጒበጥ።
24 መዓትህን በላያቸው አፍስስ፤የቍጣህም መቅሠፍት ድንገት ይድረስባቸው።
25 ሰፈራቸው ባድማ ይሁን፤በድንኳኖቻቸው የሚኖር አይገኝ፤