31 ከበሬ ይልቅ፣ቀንድና ጥፍር ካበቀለ እምቦሳም ይልቅ ይህ እግዚአብሔርን ደስ ያሰኘዋል።
32 ድኾች ይህን ያያሉ፤ ደስም ይላቸዋል፤እናንተ እግዚአብሔርን የምትሹ ልባችሁ ይለምልም!
33 እግዚአብሔር ችግረኞችን ይሰማልና፤በእስራት ያለውንም ሕዝቡን አይንቅም።
34 ሰማይና ምድር፣ ባሕርም፣በውስጣቸውም የሚንቀሳቀስ ሁሉ ያመስግኑት።
35 እግዚአብሔር ጽዮንን ያድናታልና፤የይሁዳንም ከተሞች መልሶ ይሠራቸዋልና፤ሕዝቡም በዚያ ይሰፍራል፤ ይወርሳታልም።
36 የባሪያዎቹም ዘሮች ይወርሷታል፤ስሙንም የሚወዱ በዚያ ይኖራሉ።