4 አንተ ብርሃን ተላብሰህ ደምቀሃል፤ግርማዊነትህም ከዘላለም ተራሮች ይልቃል።
5 ልበ ሙሉ የሆኑት ተዘርፈዋል፤አንቀላፍተውም ተኝተዋል፤ከጦረኞቹም መካከል፣እጁን ማንቀሳቀስ የቻለ የለም።
6 የያዕቆብ አምላክ ሆይ፤ ከተግሣጽህ የተነሣ፣ፈረስና ፈረሰኛው ጭልጥ ብለው ተኝተዋል።
7 መፈራት ያለብህ አንተ ብቻ ነህ፤በተቈጣህ ጊዜ ማን በፊትህ መቆም ይችላል?
8 አንተ ፍርድን ከሰማይ አሰማህ፤ምድርም ፈርታ ጸጥ አለች፤
9 አምላክ ሆይ፤ ይህም የሆነው አንተ የምድር ጐስቋሎችን ለማዳን፣ለፍርድ በተነሣህ ጊዜ ነው። ሴላ
10 ሰውን ብትቈጣ እንኳ ለክብርህ ይሆናል፤ከቍጣ የተረፉትንም ትገታቸዋለህ።