59 እግዚአብሔር ይህን በሰማ ጊዜ እጅግ ተቈጣ፤እስራኤልንም ፈጽሞ ተወ።
60 በሰዎች መካከል ያቆማትን ድንኳን፣የሴሎን ማደሪያ ተዋት።
61 የኀይሉን ምልክት አስማረካት፤ክብሩንም ለጠላቶቹ እጅ አሳልፎ ሰጠ።
62 ሕዝቡን ለሰይፍ ዳረገ፤በርስቱም ላይ እጅግ ተቈጣ።
63 ጐልማሶቻቸውን እሳት በላቸው፤ልጃገረዶቻቸውም የሰርግ ዘፈን አልተዘፈነላቸውም።
64 ካህናታቸው በሰይፍ ተገደሉ፤መበለቶቻቸውም ማልቀስ ተሳናቸው።
65 ጌታም ከእንቅልፍ እንደሚነቃ ተነሣ፤የወይን ጠጅ ስካር እንደ በረደለት ጀግናም ብድግ አለ።