10 ተራሮች በጥላዋ ተሸፈኑ፤ግዙፍ ዝግቦችም በቅርንጫፎቿ ተጠለሉ።
11 ቅርንጫፎቿን እስከ ባሕሩ፣ቊጥቋጦዋንም እስከ ወንዙ ዘረጋች።
12 ታዲያ ዐላፊ አግዳሚው ፍሬዋን እንዲለቅም፣ለምን ቅጥሯን አፈረስህ?
13 ዕርያ ከዱር ወጥቶ ያበለሻሻታል፤በሜዳ የሚንጋጋ እንስሳ ሁሉ ይበላታል።
14 የሰራዊት አምላክ ሆይ፤ እንግዲህ ወደ እኛ ተመለስ፤ከሰማይ ተመልከት፤ እይም፤ይህችን የወይን ተክል ተንከባከባት፤
15 ይህች ቀኝ እጅህ የተከላት ቡቃያ፣ለራስህ ያጸደቅሃት ተክል ናት።
16 እርሷም በእሳት ተቃጥላለች፤የግንባርህ ተግሣጽ ያጠፋቸዋል።