2 ለአንተ የተለየሁ ሰው ነኝና ነፍሴን ጠብቃት፤አንተ አምላኬ ሆይ፤በአንተ የታመነብህን ባሪያህን አድን።
3 ጌታ ሆይ፤ ማረኝ፤ቀኑን ሙሉ ወደ አንተ እጮኻለሁና።
4 የባሪያህን ነፍስ ደስ አሰኛት፤ጌታ ሆይ፤ ነፍሴን ወደ አንተ አነሣለሁና።
5 ጌታ ሆይ፤ አንተ ቸርና ይቅር ባይ ነህ፤ለሚጠሩህ ሁሉ ምሕረትህ ወሰን የለውም።
6 እግዚአብሔር ሆይ፤ ጸሎቴን አድምጥ፤የልመናዬን ጩኸት ስማ።
7 አንተ ስለምትመልስልኝ፣በመከራዬ ቀን ወደ አንተ እጣራለሁ።
8 ጌታ ሆይ፤ ከአማልክት መካከል እንደ አንተ ያለ የለም፤ከአንተም ሥራ ጋር የሚወዳደር ሥራ የለም።