5 በሙታን መካከል እንደ ተጣሉ፣ተገድለው በመቃብር ውስጥ እንደ ተጋደሙ፣አንተ ከእንግዲህ እንደማታስባቸው፣ከእጅህም ወጥተው እንደ ተወገዱ ሆንሁ።
6 በዐዘቅት ጥልቀት ውስጥ ጣልኸኝ፤በጨለማ ጒድጓድ ውስጥ ከተትኸኝ።
7 የቊጣህ ክብደት በላዬ ዐርፎአል፤በማዕበልህም ሁሉ አጥለቅልቀኸኛል። ሴላ
8 የሚቀርቡኝ ባልንጀሮቼን ከእኔ አራቅህ፤እንዲጸየፉኝም አደረግህ፤ተከብቤአለሁ፤ ማምለጥም አልችል፤
9 ዐይኖቼም በሐዘን ፈዘዙ። እግዚአብሔር ሆይ፤ ዘወትር ወደ አንተ እጣራለሁ፤እጆቼንም ወደ አንተ ዘረጋሁ።
10 ድንቅ ሥራህን ለሙታን ታሳያለህን?የሙታንስ መናፍስት ተነሥተው ያመሰግኑሃልን? ሴላ
11 ምሕረትህ በመቃብር ውስጥ፣ታማኝነትህስ እንጦርጦስ ይነገራልን?