28 ምሕረቴንም ለዘላለም ለእርሱ እጠብቃለሁ፤ከእርሱ ጋር የገባሁት ኪዳንም ጸንቶ ይኖራል።
29 የዘር ሐረጉን ለዘላለም፣ዙፋኑንም በሰማያት ዕድሜ ልክ አጸናለሁ።
30 “ልጆቹ ሕጌን ቢተዉ፣ደንቤን ባይጠብቁ፣
31 ሥርዐቴን ቢጥሱ፣ትእዛዜንም ባያከብሩ፣
32 ኀጢአታቸውን በበትር፣በደላቸውን በጅራፍ እቀጣለሁ።
33 ምሕረቴን ግን ከእርሱ አላርቅም፤ታማኝነቴንም አላጓድልበትም።
34 ኪዳኔን አላፈርስም፤ከአፌ የወጣውንም አላጥፍም።