1 ለእግዚአብሔር አዲስ ዝማሬ ዘምሩ፤ምድር ሁሉ፤ ለእግዚአብሔር ዘምሩ።
2 ለእግዚአብሔር ዘምሩ፤ ስሙንም ባርኩ፤ማዳኑንም ነጋ ጠባ አውሩ።
3 ክብሩን በሕዝቦች መካከል፣ድንቅ ሥራውንም በሰዎች ሁሉ ፊት ተናገሩ።
4 እግዚአብሔር ታላቅ ነውና፤ ውዳሴም የሚገባው ነው፤ከአማልክትም ሁሉ በላይ ሊፈራ ይገባዋል።
5 የሕዝብ አማልክት ሁሉ ጣዖታት ናቸው፤ እግዚአብሔር ግን ሰማያትን ሠራ።
6 ክብርና ግርማ በፊቱ ናቸው፤ብርታትና ውበትም በመቅደሱ ውስጥ አሉ።