5 የሕዝብ አማልክት ሁሉ ጣዖታት ናቸው፤ እግዚአብሔር ግን ሰማያትን ሠራ።
6 ክብርና ግርማ በፊቱ ናቸው፤ብርታትና ውበትም በመቅደሱ ውስጥ አሉ።
7 የሕዝቦች ወገኖች ሆይ፤ ለእግዚአብሔር ስጡ፤ክብርንና ብርታትን ለእግዚአብሔር ስጡ።
8 ለስሙ የሚገባ ክብርን ለእግዚአብሔር ስጡ፤ቍርባንን ይዛችሁ ወደ አደባባዩ ግቡ።
9 በተቀደሰ ውበት ለእግዚአብሔር ስገዱ፤ምድር ሁሉ፤ በፊቱ ተንቀጥቀጡ።
10 በሕዝቦች መካከል፣ “እግዚአብሔር ነገሠ” በሉ፤ዓለም በጽኑ ተመሥርታለች፤ አትናወጥም፤እርሱ ለሕዝቦች በእኩልነት ይፈርዳል።
11 ሰማያት ደስ ይበላቸው፤ ምድርም ሐሤት ታድርግ፤ባሕርና በውስጧ ያለው ሁሉ ያስተጋባ፤