7 ለተቀረጸ ምስል የሚሰግዱ፣በጣዖታትም የሚመኩ ሁሉ ይፈሩ፤እናንተ አማልክት ሁሉ፤ ለእርሱ ስገዱ።
8 እግዚአብሔር ሆይ፤ ስለ ፍርድህ፣ጽዮን ሰምታ ደስ አላት፤የይሁዳም ሴት ልጆች ሐሤት አደረጉ።
9 እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ በምድር ሁሉ ላይ ልዑል ነህና፤ከአማልክትም ሁሉ በላይ እጅግ ከፍ ያልህ ነህ።
10 እግዚአብሔርን የምትወዱ ክፋትን ጥሉ፤እርሱ የታማኞቹን ነፍስ ይጠብቃልና፤ከዐመፀኞችም እጅ ይታደጋቸዋል።
11 ብርሃን ለጻድቃን፣ሐሤትም ልባቸው ለቀና ወጣ።
12 እናንተ ጻድቃን በእግዚአብሔር ደስ ይበላችሁ፤ቅዱስ ስሙንም አመስግኑ።