1 እግዚአብሔር ሆይ፤ ጸሎቴን ስማ፤ጩኸቴም ወደ አንተ ይድረስ።
2 በመከራዬ ቀን፣ ፊትህን ከእኔ አትሰውር፤ጆሮህን ወደ እኔ አዘንብል፤በጠራሁህ ቀን ፈጥነህ መልስልኝ።
3 ዘመኔ እንደ ጢስ ተኖ አልቆአልና፤ዐጥንቶቼም እንደ ማንደጃ ግለዋል።
4 ልቤ ዋግ እንደ መታው ሣር ደርቆአል፤እህል መብላትም ዘንግቻለሁ።
5 ከጩኸቴ ድምፅ የተነሣ፣ዐጥንቴ ከቈዳዬ ጋር ተጣበቀ።
6 የምድረ በዳ እርኩም መሰልሁ፤በፍርስራሽ መካከል እንዳለ ጒጒት ሆንሁ።
7 ያለ እንቅልፍ አድራለሁ፤በቤቴ ጒልላት ላይ እንዳለ ብቸኛ ወፍ ሆንሁ።